Duration 5:34

️ ፋኖ ሞላ ደስየ /Fano

11 464 watched
0
480
Published 10 Dec 2021

በደሴ ድል ጓድ ሞላ ደስየ ሲታዎስ **************************** ሞላ ደስየን የተዋወቅኩት በፈተና ጊዜ ነው። የልብ ጓደኛው በነበረው የፍ/ቤት ክርክር በሙያየ እንዳግዘው የኔዋ የጁ ገነት "ወልድያ" ከተማ ጎንደር በር አካባቢ በሚገኝ እንድ ሆቴል ተገናኝተን ስናወራ ነው። እናም በነበረን ቆይታ ሰው አክባሪነቱ፣ አድማጭነቱና ትህትናው ይገርመኝ ነበር። በሚንገዳገደው የሃገራችን የፍትህ ስርዓት ውስጥ በፍ/ቤቶቻችን ላይ ያለው እምነት ያስቀናል። ጉልበት ባለው ጊዜ ለሃገሪቱ ህግ ያሳየው ተገዥነት ያስጎመዣል። አለ አይደል ሃገሩን በድሎትም በችግርም ስዓት ከልቡ ሲዎዳት ሳይ መንፈሳዊ ቅናት አደረብኝ! በሌላ በኩል ለጓደኝው ያለው ታማኝነት! ሰው በዚህ ልክ ራሱን እንዴት ይወዳል በሚባለው ደረጃ ልክ ጓደኛውን ሲዎድ ሳየው ገረመኝ። ለነገሩ ትርፉ መላላጥ ነው እንጅ ለትግል ጓዱና ለሃገሩ በተጫረ ቀብር ውስጥ እኔ ሙቸ እናንተ ኑሩ ብሎ ህይወቱን ሰውቶ ሃገሩንና ጓዱን ላተረፈ ሰው ጓደኛውን ይወድ ነበር ብየ ለመግለጥ ብሞክር በምን ቃል ልፅፈው እችላለሁ!? በምንም! ጊዜ ደግ ነው፤ ተራ ተረት የመሰሉኝን ተረተቶች እውን መሆናቸውንም አረጋገጥኩ። እናም በዚህ አጋጣሚ "ለጓደኛው ሞች ነው" የሚባለው ተረት ላይ ላደረስኩበት "ፌዝ" ይቅርታ ማለት ሳይኖርብኝ አይቀርም። ******************** ደሴ ቦሩ ሜዳ ላይ ጦርነቱ ግሎ ሰማይ መሬቱ ንዳድ ላይ እንዳለ የወሎ ፋኖ ካምፕ ወዳደረጉበት ቦታ ጎራ እንዳልኩ ጓድ ሞላ ወደ አውደውጊያው ሊሆድ ከነሙሉ ትጥቁ ከካምፑ በራፍ አካባቢ ድንገት አግኝቸው ሰላም ካልኩት በኋሃላ ውስጤን ባር ባር አለው መሰለኝ ትንሽ ለማዋራት አስቤ ስለ ውቦ ደሴና ስለ እማማ ኢትዩጵያ ሲሉ ከራያ እስከ ወሎ ግምባር ስለተሰው ጓዶች አንስቸ ስጠይቀው ስማማ አለኝ፤ "እነሱማ ሸክማቸው ቀሏል ለሃገራቸውና ወገናቸው የድርሻቸውን አበርክተው ተሰውተዋል፤ አሁን እዳው የኔና ያንተ የቀሪዎቹ ነው። ቀሪን ይጭነቀው" ብሎኝ ተሰናበተ። ከእኔ ጋር ያደረግነው የመጨረሻ ስንብት መሆኑ ነው።😢 ******************* እናም ሁሌ "ደሴን" ሳስብ የጓድ ሞላ "ቀሪን ይጭነቀው" የሚለው ቃል አእምሮየ ውስጥ ያቃጭልብኛል። ከነሱ ህልፈት በኋላ ደሴ በወራሪዎች እጅ ወድቃ በቆየችባቸው ጊዜያት ቃሉ እንደ እግር እሳት ሲያቃጥለኝ ቆይቷል። ጊዜው ደርሶ ዛሬ የኔዋ ደሴ ነፃ ስትዎጣ፤ ከጫፍ ጫፍ ያሉ ቀሪ ወንድምና እህቶች ደሴን ነፃ አውጥተዋታል ብየ ብነግረው ምንኛ በወደድኩ። ከንቱ ምኞት! ግን ግን ደማችሁ በከንቱ አንዳይቀር የሃገራችን ቁስሏ እንዲሽር እኛ ቀሪዎቿ ስለ ቀሪው የኢትዩጵያ ክፈል እና በጨካኞች ስር ስላሉ ወገኖች እንደሚጨንቀንና በተባበረ ክንዳችን ነፃ ለማውጣት የናንተ ብርታት ያበረታን መሆኑን አለም ይወቀው! **************** ከሃይቅ--መርሳ--ወልድያ--ቆቦ በችርቻሮ ከአለማጣ እስከ መቀሌ በጃምላ ነፃ ሳይወጡ ነፃነት የለም! የአማራ ህዝባዊ ሀይል / ፋኖ/ | Wollo Tube /ወሎ ቲዩብ |

Category

Show more

Comments - 91